Mahilete Tsige ማኅሌተ ጽጌ APK
Informations
Version 2.3 (#23)
Mise à jour 15 May 2019
Taille APK 6 MB
Nécessite Android Android 4.0+ (Ice Cream Sandwich)
Proposée par Getahun Amare Ayalew
Catégorie App de Livres et références Gratuits
App id com.goranda.MahileteTsige.AOVWRGEMFFMCMATLJY
Notes d'auteur ማኅሌተ ጽጌ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጸሎት መጽሐፍ ነው ::
Captures d'écran
Cliquez sur l'image pour la voir en taille réelle
Tableau des matières
Dernières mises à jour
Nouveautés sur Mahilete Tsige ማኅሌተ ጽጌ 2.3
Information About our products Added
Description
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ኃይለ ቃልን ከትርጓሜ, ትርጓሜን ከምሥጢር እንዲሁም ደግሞ ምሥጢርን ከዜማ ጋር አስተባብረውና አስማምተው የሚደርሱ ሊቃውንት ባለቤት ናት. በ 5 ኛው መ.ክ.ዘመን የተነሣው ታላቁ ሊቅቅዱስ ያሬድ አምስቱን ጸዋትወ ዜማ ሲደርስ በ 14 ኛው መ.ክ.ዘመን የተነሣው አባ ጊዮርጊስ ደግሞ ሰዓታትን ደርሷል. በዚሁ ዘመን አባ ጊዮርጊስ ጋር ጥልቅ መንፈሳዊ ፍቅር የነበረው አባ ጽጌ ድንግል "ማኅሌተ ጽጌ" የተባለውን ድርሰት ደርሷል.
ማኅሌተ ጽጌ ግጥማዊ አካሔድ ያለው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ድርሰት ነው. ይህ ድርሰት በማንኛውም ጊዜ የሚጸለይ ቢሆንም በተለየ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውለው ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ድረስ ባለው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የስደት ዘመን ነው. በዚህ ወቅት በየሳምንቱ እሑድ ሌሊት በሙሉ የእመቤታችንን ከልጇ ጋር ወደ ግብፅ መሰደድና መንከራተት እያሰቡ የሚደረስ ምሥጋናና ጸሎት ነው.
በዘመነ ጽጌ ቅዱስ ያሬድ ከደረሰው ድጓ በተጨማሪ ከላይ እንደተጠቀሰው በ 14 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሣ አባ ጽጌ ድንግል ከዚሁ ዘመን ጋር የተያያዘ ድርሰት ደርሷል. ይህ ድርሰት በግጥም መልክ የተደረሰ በአብዛኛው አምስት ስንኞች ያሉት ሲሆን ብዛቱም 15 ዐ ያክል ነው. ይህም ድርሰት «ማኅሌተ ጽጌ» በመባል የሚታወቀው ነው. ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኘው ሁሉ ማኅሌተ ጽጌም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመሰለ የሚያስረዳ ድርሰት ነው. እርሷን በአበባ ሲመስል ልጇን በፍሬ እርሷን በፍሬ ሲመስል ደግሞ ልጇን በአበባ እየመሰለ ይናገራል. ነቢዩ ኢሳይያስ «ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዓርግ ጽጌ እምጉንዱ; ከእሴይ ግንድ በትርይወጣል; ከሥሩም ቁጥቋጦ ያፈራል» /ኢሳ.11 1/ ብሎ ከእሴይ ዘር የምትገኘውን እመቤታችንን በበትር ከርሷ የሚገኘውን ክርስቶስን ደግሞ በጽጌ መስሎ ትንቢቱን ተናግሯል. አባ ጽጌ ድንግልም ድርሰቱን በዚሁ አንጻር በመቀመር እያንዳንዱን መልክዕ እመቤታችንንና ልጇን አስተባብሮ በጽጌና በፍሬ በመመሰል የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ በምሥጢር በታሪክ, በጸሎትና በመሳሰለው መልክ ድንቅ በሆነና በተዋበ ሁኔታ አዋሕዶ ደርሶታል.
Notes et avis
Note: 4.4 sur 5 · Less than 100 votes
(*) est nécessaire
Versions précédentes
Vous aimerez peut-être aussi
Ethiopian Orthodox Calendar APK
Afaan Oromo Bible - Macaafa Qulqulluu APK
Du même développeur
Metsihafe Seatat መጽሐፈ ሰዓታት APK
Geez Amharic Orthodox Bible 81 APK
Melka Mariam We Melka Eyesus APK
Applications les plus téléchargées
فیلتر شکن جدید و قوی،فیلتر شکن قوی و پرسرعت رایگان APK