Mahilete Tsige ማኅሌተ ጽጌ APK
اطلاعات
نسخه 2.3 (#23)
به روز شده 2019-05-15
اندازه پرونده APK 6 MB
نسخه Android مورد نیاز Android 4.0+ (Ice Cream Sandwich)
برنامه نویس Getahun Amare Ayalew
رده کتابها و منابع (برنامه)
ID com.goranda.MahileteTsige.AOVWRGEMFFMCMATLJY
یادداشت های توسعه دهنده ማኅሌተ ጽጌ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጸሎት መጽሐፍ ነው ::
تصویر نماگرفت
برای دیدن اندازه اصلی روی عکس کلیک کنید
فهرست مطالب
قابلیت های جدید
تازه چه خبر در Mahilete Tsige ማኅሌተ ጽጌ 2.3 است
Information About our products Added
شرح
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ኃይለ ቃልን ከትርጓሜ، ትርጓሜን ከምሥጢር እንዲሁም ደግሞ ምሥጢርን ከዜማ ጋር አስተባብረውና አስማምተው የሚደርሱ ሊቃውንት ባለቤት ናት. በ 5 ኛው መ.ክ.ዘመን የተነሣው ታላቁ ሊቅቅዱስ ያሬድ አምስቱን ጸዋትወ ዜማ ሲደርስ በ 14 ኛው መ.ክ.ዘመን የተነሣው አባ ጊዮርጊስ ደግሞ ሰዓታትን ደርሷል. በዚሁ ዘመን አባ ጊዮርጊስ ጋር ጥልቅ መንፈሳዊ ፍቅር የነበረው አባ ጽጌ ድንግል "ማኅሌተ ጽጌ" የተባለውን ድርሰት ደርሷል.
ማኅሌተ ጽጌ ግጥማዊ አካሔድ ያለው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ድርሰት ነው. ይህ ድርሰት በማንኛውም ጊዜ የሚጸለይ ቢሆንም በተለየ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውለው ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ድረስ ባለው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የስደት ዘመን ነው. በዚህ ወቅት በየሳምንቱ እሑድ ሌሊት በሙሉ የእመቤታችንን ከልጇ ጋር ወደ ግብፅ መሰደድና መንከራተት እያሰቡ የሚደረስ ምሥጋናና ጸሎት ነው.
በዘመነ ጽጌ ቅዱስ ያሬድ ከደረሰው ድጓ በተጨማሪ ከላይ እንደተጠቀሰው በ 14 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሣ አባ ጽጌ ድንግል ከዚሁ ዘመን ጋር የተያያዘ ድርሰት ደርሷል. ይህ ድርሰት በግጥም መልክ የተደረሰ በአብዛኛው አምስት ስንኞች ያሉት ሲሆን ብዛቱም 15 ዐ ያክል ነው. ይህም ድርሰት «ማኅሌተ ጽጌ» በመባል የሚታወቀው ነው. ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኘው ሁሉ ማኅሌተ ጽጌም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመሰለ የሚያስረዳ ድርሰት ነው. እርሷን በአበባ ሲመስል ልጇን በፍሬ እርሷን በፍሬ ሲመስል ደግሞ ልጇን በአበባ እየመሰለ ይናገራል. ነቢዩ ኢሳይያስ «ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዓርግ ጽጌ እምጉንዱ؛ ከእሴይ ግንድ በትርይወጣል؛ ከሥሩም ቁጥቋጦ ያፈራል» /ኢሳ.11 1/ ብሎ ከእሴይ ዘር የምትገኘውን እመቤታችንን በበትር ከርሷ የሚገኘውን ክርስቶስን ደግሞ በጽጌ መስሎ ትንቢቱን ተናግሯል. አባ ጽጌ ድንግልም ድርሰቱን በዚሁ አንጻር በመቀመር እያንዳንዱን መልክዕ እመቤታችንንና ልጇን አስተባብሮ በጽጌና በፍሬ በመመሰል የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ በምሥጢር በታሪክ، በጸሎትና በመሳሰለው መልክ ድንቅ በሆነና በተዋበ ሁኔታ አዋሕዶ ደርሶታል.
رأی و نظرات
رتبه: 4.4 / 5 · Less than 100 رأی
(*) مورد نیاز است
نسخه های قبلی
مشابه
Ethiopian Orthodox Calendar APK
Afaan Oromo Bible - Macaafa Qulqulluu APK
بیشتر از Getahun Amare Ayalew
Metsihafe Seatat መጽሐፈ ሰዓታት APK
Geez Amharic Orthodox Bible 81 APK
Melka Mariam We Melka Eyesus APK
بیشترین بارگیری برنامه ها و بازی ها
فیلتر شکن جدید و قوی،فیلتر شکن قوی و پرسرعت رایگان APK