ሶስቱ መሰረቶች APK
App information
Version 1.0 (#1)
Updated 2020-08-26
APK Size 2.9 MB
Requires Android Android 2.1+ (Eclair)
Offered by Abdulsemed
Category Free Books & Reference App
App id appinventor.ai_abuadnanabumeriem.UsuluSelasa
Developer's notes الأُصُولُ الثَّلاثَةُሶስቱ መሰረቶችሸይኽሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወህሃብረሒመሁላህ
Screenshot
Click on the image to see full size
Table of contents
Editor's review
Download the latest ሶስቱ መሰረቶች application, version 1.0, compatible with Windows 10/11 (using emulators such as Bluestacks), Android devices. This free Books & Reference app is developed by Abdulsemed and is easy to download and install.
Previous versions, including 1.0, are also available. If you need help or have any problems, please let us know.
Description
ሶስቱ መሰረቶች
ሸይኽ
ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወህሃብ
ረሒመሁላህ
(1115 – 1206 ዓ.ሂ.)
መግቢያ
“አልኡሱሉ አሥሠላሣህ” እና “አልቀዋዒዱል አርበዕ” ኪታቦች በሱንኒው አለም ባሉ ሙስሊሞች ዘንድ ሰፊ እውቅና እና ተቀባይነት ያላቸው ኪታቦች ናቸው፡፡ ኪታቦቹ በውስጣቸው ከያዙት አንገብጋቢ የተውሒድ መልእክት በተጨማሪ አቀራረባቸው በራሱ እራሱን የቻለ ትልቅ ስርኣተ-ትምህርት ነው፡፡ እያንዳንዱ ነጥብ በቁርኣናዊ ወይም ሐዲሣዊ ማስረጃ መደገፉ በዚህ ስርኣተ- ትምህርት ውስጥ ያለፈ ትውልድ የትኛውንም እምነት ነክ ጉዳይ ያለ ማስረጃ ሊቀበል እንደማይገባው ፅኑ መልእክት አለው፡፡
በትርጉም ስራዬ ላይ በኪታቦቹ ውስጥ የተጠቀሱ የቁርኣን አንቀፆችን፣ ሐዲሦችን እና የዑለማእ ንግግሮችን መገኛቸውን ያሰፈርኩ ሲሆን ሐዲሦቹን ቡኻሪና ሙስሊም ከዘገቧቸው ውጭ ባሉት ላይ የታላቁን ሙሐዲሥ የሸይኹል አልባኒን ብይኖች አስፍሬያለሁ፡፡ አልፎ አልፎ ሀሳቦችን ያብራራሉ ብዬ ያሰብኳቸውን ማስታወሻዎች ከግርጌ አስፍሬያለሁ፡፡
ኪታቦቹን ለመማር ማስተማር ይበልጥ እንዲያግዝ በማለም ሙሉ ትርጉም ብቻ ከማድረግ ይልቅ ዐረብኛውን መልእክት ካሰፈርኩ በኋላ ቀጥሎ ትርጉሙን ያስከተልኩ ሲሆን ለጀማሪዎች እንዲያግዝ በማሰብም የዐረብኛ አናባቢ ምልክቶች (ሐረካት) እንዲኖሩ አድርጌያለሁ፡፡
ያለንበት ዘመን እንደ አሕባሽ ያሉ የጥፋት ሃይሎች ኢስላማችንን ለመናድ፣ ህዝባችንን በብልሹ እምነቶች ለመበከል ቆርጠው የተነሱበት ዘመን እንደመሆኑ ወላጆች ለልጆቻቸው ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትኩረት ሊሰጡ የሚገባቸው ጊዜ ነው፡፡ ሁሌ እንደ አሸን እየፈሉ ያሉ የአስተሳሰብ ወረራዎችን ለመመከት ንቃተ-ህሊናን ማዳበር ቀዳሚው ምርጫ እንደመሆኑ ወላጆች ይህንን የትልቅ ዓሊም ትልቅ ስራ እና መሰል ጤናማ ኪታቦችን እየመረጡ ለልጆቻቸው በማቅረብ ልጆች ከምንም በላይ፣ ከምንም ቀድሞ የጌታቸውን ሐቅ እንዲያውቁ ሊያግዟቸውና እራሳቸውን ከጥፋት የሚጠብቁበት እውቀት ሊያስታጥቋቸው ይገባል፡፡ ዛሬ ላይ ለተውሒድ ግንዛቤውና ፍቅሩ ያለው ትውልድ ማፍራታችን በሂደት ጠንካራ ህዝብ ለመገንባት ፅኑ መሰረት ይሆነናል፡፡
መፅሐፉ በቀጣይ እትም በተሻለ መልኩ ይወጣ ዘንድ እርምት ወይም ሀሳብ ያለው ሰው ለሚሰጠኝ ጥቆማ አስቀድሜ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡
ሙሐመድ አሕመድ ሙነወር
ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወህሃብ አላህ ይዘንላቸውና በ 1115 ዓመተ-ሂጅራ ተወልደው በ 1206 ነው የሞቱት፡፡ ቁርኣንን ገና አስር አመት ሳይሞላቸው የሐፈዙ ሲሆን ዒልም ፍለጋ ከትውልድ ቀያቸው በመውጣት ወደ መካ፣ መዲናህ፣ አልአሕሳእ፣ በስራ፣ በግዳድ ተጉዘዋል፡፡ የተወለዱትም የሞቱትም ዑየይናህ ውስጥ ነው፣ በሳዑዲ ዐረቢያ ነጅድ ክልል፡፡ ለደዕዋ የሚያግዛቸውን እውቀት ከገበዩ በኋላ በቀጥታ ወደ ደዕዋው መስክ በመግባት ህይወታቸውን በዚሁ ላይ አሳልፈዋል፡፡ የደዕዋቸው ቀዳሚ ትኩረትም በዘመናቸው በሰፊው የተንሰራፋውን በኢስላም ስም የሚፈፀም የባእድ አምልኮ መጋፈጥ ነበር፡፡ የተውሒድ ዘመቻቸው በአላህ እገዛ ፍሬ አፍርቶ የልፋታቸውን ውጤት በአይናቸው ለማየት በቅተዋል፡፡
ሸይኹ ዐቂዳን ማስተካከል ላይ ያነጣጠሩ በርከት ያሉ ኪታቦችን ጥለው ያለፉ ሲሆን ተማሪዎቻቸውና ወራሾቻቸውም ሀላፊነታቸውን ተረክበው የድርሻቸውን ተወጥተዋል፡፡
ሸይኹ - አላህ ይዘንላቸውና - ጠላቶቻቸው እንደሚቀጥፉባቸው ከቁርኣንና ከሐዲስ ያፈነገጠ እንግዳ አስተሳሰብ አላመጡም፡፡ ለእያንዳንዱ ንግግሮቻቸው የቁርኣንና የሐዲስ ማስረጃ መጥቀሳቸውም ይህንን ሐቅ በሚገባ ያስረዳል፡፡ በየመሀሉ የቀደምት ዑለማዎችን ንግግሮች ጣል ማድረጋቸውም በቀደምቶቹ ፍኖት ላይ የሚጓዙ እንጂ አዲስ አስተሳሰብ ጠንሳሽ እንዳልሆኑ በቂ ምስክር ነው፡፡
App permissions
ሶስቱ መሰረቶች 1.0 APK requires following permissions:
Allows applications to open network sockets.
Allows applications to access information about networks.
Allows applications to access information about Wi-Fi networks.
Ratings and Reviews
Rating: 4.6/5 based on 1+ reviews
(*) is required
5 ★ ማሻአሏህ ደስ ይላል በርቱ ወንድሞቻችን አላህ ጀዛችሁን ይክፈል በቀላል ተውሂድን ተደራሽ ማድረጋችሁ ያበረታታል
5 ★ ጀዛኩም ላህ ከይረን አላህ መልካም ስራችሁን ወዶ ይቀበላችሁ እኛም በሰማነዉ አላህ ተጠቃሚ ያድረገን ።
5 ★ ማሻ አላህ ደስ ይላል። ጀዛከላህ ኸይር የመጀመርያው ዳውንሎድ ያደረኩት 🙄😊😊😊
5 ★ أستاذ جزاك الله خيرا في دنيا والأخير .الله يحفظكم!!
5 ★ ጀዛከ አላህ ኡስታዝ በጣም አሪፍ ነው አላህ ይጠብቃችሁ
5 ★ awesome app Jazak ALLAH keyren
5 ★ አላህ እውቀታችሁን ይጨምርላችሁ አላህ ይጠብቃችሁ ሠላማችሁን ያብዛላችሁ
4 ★ Masha allah endet des endemil srachihu alah ychemrlachihi
5 ★ ማሻአላህ አላህ ይጨምርልህ በእውቀት ላይ እውቀት ሃትማህም አላህ ያሳምርልህ ኡስታዛችን
5 ★ Masha allah jezakumula keyr
5 ★ ኣላህ ኸይር ጀዛቹህን ይክፈላቹህ
5 ★ በርቱ ይበል የሚያሰኝ ነው
5 ★ ማሻአላህ አላህ ይጨምርላቹ
5 ★ Jazake allahe hayre
1 ★ ማሻአላህ ጀዛ ኪላህ
Previous versions
Similar to ሶስቱ መሰረቶች
More from Abdulsemed
Top download apps
فیلتر شکن جدید و قوی،فیلتر شکن قوی و پرسرعت رایگان APK